አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የጃማይካ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሪው ሆልነስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም ሀገራቸው ጃማይካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ታሪካዊ ወዳጅነት እና ትስስር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጠው ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በጃማይካ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ለሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ትብብርን የበለጠ ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አመልክተዋል፡፡
ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሁለተኛው የሥራ ዘመናቸው ሙሉ ስኬትን፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ጽኑ ብልጽግናን በመመኘት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

