Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየማቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ላላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ከፍተኛ ክብር እንደምትሰጥ አውስተው፤ የሁለቱን ሀገራት ትብብርና ወዳጅነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕንድ የመንግሥት ከፍተኛ ኃላፊነት ውስጥ ለ25 ዓመታት በማገልገል የብር ኢዮቤልዩ በዓላቸውን እያከበሩ ለሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትናንትናው ዕለት የደስታ መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አመስግነው፤ ቀጣይ የኃላፊነት ጊዜያቸው ስኬታማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version