አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
በዚህም መሰረት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው እንዲሰየሙ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በምክር ቤቱ ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ

