Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ማካሄድ ጀምሯል፡፡

በመደበኛ ስብሰባው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

1. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
2. አቶ አዲሱ አረጋ  – የግብርና ሚኒስትር

3. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) – የገንዘብ ሚኒስትር
4. አቶ መሃመድ እድሪስ – የመከላከያ ሚኒስትር

5. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) – የትምህርት ሚኒስትር
6. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ – የፍትሕ ሚኒስትር

7. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ – የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
8. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር

9. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) – የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
10. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) – የጤና ሚኒስትር

11. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
12. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ – የገቢዎች ሚኒስትር

13. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን – የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
14. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር

15. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ – የማዕድን ሚኒስትር
16. አቶ ሳዳት ነሻ – የሎጂስቲክስ ሚኒስትር

17. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ – የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
18. አቶ ሙሳ አደም – የሰላም ሚኒስትር

19. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ – የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
20. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር

21. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) – የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
22. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) – የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል፡፡

የአዲሱ የመደመር መንግሥት ተሿሚ ሚኒስትሮችም በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡

#የመደመርመንግሥት

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version