አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በወጪ ንግድ የተገኘው ስኬት ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ያስሚን ወሃብረቢ፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላት ሹመት አጽድቋል፡፡
በዚህም ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
ሚኒስትሯ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ ፥ በተሰጠኝ ሀገራዊ ኃላፊነት ለማገልገል ትልቅ አደራ ወስጃለሁ፤ ኃላፊነቴንም በትጋትና ህዝብን በታማኝነት በማገልገል እወጣለሁ ብለዋል፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ዘርፍ የዘመነ የተቀላጠፈና ተደራሽ የሆነ የንግድ ስርዓትን ከመዘርጋት አኳያ በፌዴራል ደረጃ የሚሰሩ ስራዎች ከክልሎች ጋር ተሳስረው ይቀጥሉ ዘንድ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቅንጅት እንሰራለን ነው ያሉት።
በዘርፉ በወጪ ንግድ የተገኘው ስኬትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለው ለዚህም በተነሳሽነት እንሰራለን ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
#የመደመርመንግሥት
በአመለወርቅ ደምሰው
በወጪ ንግድ የተገኘው ስኬት ተጠናክሮ ይቀጥላል – ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ

