Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

829 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 829 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል አለ የጉምሩክ ኮሚሽን፡፡
ኮሚሽኑ ከመስከረም 21 እስከ 27 ቀን 2019 ዓ.ም ባደረገው ክትትል ነው 829 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች የያዘው፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት፣ ነዳጅና የውጭ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
የገቢና ወጪ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ድሬድዋ፣ ሞያሌ እና አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዙ ተጠቁሟል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ሕብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና ብርበራ መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 25 ተጠርጣሪዎች እና 14 ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው የተገለጸው፡፡
Exit mobile version