አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) እና ልዑካቸው የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ (ዶ/ር) ለልዑካን ቡድኑ ባደረጉት ገለጻ፣ ተቋሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የፈጠራ ሥራዎችን በማበልጸግ በሀገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ እያበረከተ ያለውን ስትራቴጂካዊ ተግባራት አብራርተዋል።
ኢንስቲትዩቱ በጤና፣ በግብርና እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዘርፎች እያመጣ ያለውን ተጨባጭ ለውጥም ለልዑካኑ አስረድተዋል።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሻንካር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩት የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎችን አድንቀዉ ሀገሪቱ ለኤ.አይ ቲክኖሎጂ በዚህ ደረጃ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑ ከቴክኖሎጂው ዘርፍ ተጠቃሚ ለመሆን ያላትን ቁርጠኛ አቋም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

