አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰንደቅ ዓላማ የሕዝብ አንድነት፣ የሉዓላዊነትና የጋራ ርዕይ መገለጫ ነው አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር)
19ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በሲዳማ ክልል በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል።
መሳይ ሀይሉ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ ሰንደቅ ዓላማ የሕዝብ አንድነት፣ የሉዓላዊነትና የጋራ ርዕይ መገለጫ ነው ብለዋል።
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል የዜጎችን ኃላፊነት ጭምር የሚያስታውስ በመሆኑ፣ ሁሉም ዜጋ የሃገርን ምልክቶች በአክብሮት በመያዝ ለሰላም፣ ለልማትና ለሀገር ግንባታ በጋራና በትብብር መስራት አለበት ሲሉ አመልክተዋል።
ዜጎች ልዩነቶችን በማክበር አንድነታቸውን በማጠናከር ለጋራ ብልጽግና በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።
#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

