Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሰንደቅ ዓላማ ለሀገር ሉዓላዊነት የተከፈለ ውድ ዋጋ ማሳያ ነው – ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሰንደቅ ዓላማ ለሀገር ሉዓላዊነት የተከፈለ ውድ ዋጋ ማሳያ ነው አሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አስካለች አልቦሮ።

19ኛው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

አፈ ጉባኤ አስካለች አለቦሮ በዚሁ ወቅት ፥ ሰንደቅ ዓላማችን የሀገራችንን ሉዓላዊነት፣ ነፃነት፣ አንድነት እና የጋራ ማንነት የሚወክል ታላቅ ምልክት ነው ብለዋል።

የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር ሰላማችንን በመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ በመትጋት ሊሆን ይገባል ነው ያሉት።

#ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Exit mobile version