Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በአይ ኤም ኤፍና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፈ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በ2026ቱ የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፈ ነው።

ዓመታዊ ስብሰባዎቹ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት፣ ከልማት አጋሮች እና ከሌሎች ሀገራት ፖሊሲ አውጪዎች ጋር በኢትዮጵያ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እድል የሚፈጥሩ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ስብሰባው አጋርነቶችን ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ዕድገቶች ላይ እይታዎችን ለመለዋወጥ የሚያግዝ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version