አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ.ኤም.ኤፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ።
በብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በታይላንድ ባንኮክ ዛሬ በተጀመረው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ.ኤም.ኤፍ) እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ዘይን ዘይዳን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ ላይ ያተኮረ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ መረጃ ያሳያል፡፡
በምክክሩ እስካሁን በሪፎርሙ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለመገምገም፣ የቅርብ ጊዜ የኢኮኖሚ ሁኔታዎችን ለመዳሰስ እና በቀጣይ በሚተገበሩ የሪፎርም ሥራዎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ለመለየት ማስቻሉ ተመላክቷል።
ሁለቱ ወገኖች የማክሮ ኢኮኖሚ ዘላቂነትን በማጠናከር ለአካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት የሚያስፈልጉ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

