Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መቐለ ከተማ ወደ ቀደመው ሰላሟ ተመልሳለች – የከተማዋ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መቐለ ከተማ ሰላሟ ተመልሶ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች አሉ የከተማዋ ነዋሪዎች፡፡

ከዚህ በፊት ህገወጡ ቡድን በመቐለና በሌሎች የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሲሰራ መቆየቱን ነዋሪዎቹ አንስተዋል፡፡

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በመቐለ ከተማ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት÷ በቅርቡ ህገወጡ የህወሃት ቡድን በፈጠረው ሁከት ምክንያት የከተማዋ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ታውኮ ነበር፡፡

አሁን ግን መንግሥት በሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራ ከተማዋ ወደቀደመው ሰላሟ መመለሷን ነው የገለጹት፡፡

ከሰላም የሚበልጥ ምንም ነገር የለም ያሉት ነዋሪዎቹ፤ የከተማዋ ሰላም ወደነበረበት በመመለሱና የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ያለምንም ስጋት መከወን በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ከፌዴራል መንግሥትና በየደረጃው ካሉ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የከተማዋቸውን ሰላም ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

Exit mobile version