Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራንቲሼክ ሩዚችካ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ በኢትዮጵያና የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት መካከል ሊኖር ስለሚችለው የትብብር ማዕቀፍ እና አጋርነት መክረዋል።
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ውጤታማና አስተማማኝ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ለማከናወን በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥ እና የማስረጃ ሥርዓት ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልተዋል።
ኢትዮጵያ የመረጃ ሥርዓቶቿን ለማጠናከር እየሠራች መሆኗን የገለጹት ሚኒስትሯ ከድርጅቱ ጋር የሚደረገው ትብብር ይህንኑ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ማመልከታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።
የዓለም አቀፉ የኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራንቲሼክ ሩዚችካ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ እንደሚያደንቁ ገልጸው ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
Exit mobile version