አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ዘመኑን ሙሉ የሙጥኝ ያለው የሴራና ሰላም ጠል የፖለቲካ መስመር የትግራይን ህዝብ ለአስከፊ መከራና እልቂት በተደጋጋሚ ሲዳርገው ይስተዋላል።
ይህ አካሄድ ድርጅቱ ካከተመለት ህልውናው ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት፣ የሰላም መንገዶችን ከመከተል ይልቅ ሀገር አፍራሽ እና ጠብ አጫሪ ድርጊቶችን ከመሰንዘር አለመቦዘኑ ፍጻሜውን እያፋጠነው ይገኛል፡፡
ይህ የጥፋት ኃይል የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት እንዲሁም ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ሰላምን ለማስፈን ያመቻቿቸውን መንገዶች እንዲሁም የተፈረሙ ስምምነቶችን በሙሉ በመጣስ ወደ ግጭት የሚያመሩ ትንኮሳዎችን በማድረግ ተጠምዶ ሰንብቷል።
ድርጅቱ ሰላማዊ ውይይቶችንና ስምምነቶችን እንደ ሽንፈት በመቁጠር፣ ለማይቀረው ወታደራዊ ሽንፈት በቅቷል፡፡
በየጊዜው የሚፈጸሙ ጠብ አጫሪ ድርጊቶች እና ሀገራዊ አንድነትን የሚሸረሽሩ እንቅስቃሴዎች፣ የትግራይን ህዝብ ከልማት መንገድ ወደኋላ መጎተቱ የቡድኑን አጥፊ ዓላማ እና ህዝብ ጠልነት በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው።
በትግራይ ክልል ዘላቂ ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ እንዲረጋገጥ ተዋቅሮ ወደ ስራ የገባውን ህጋዊ ጊዜያዊ አስተዳደር በኃይል በማስወገድና እገታን በመፈጸም የህወሓትን ህገወጥነትና ራስ ወዳድ አካሄድ ቁልጭ አድርጎ ለዓለም አሳይቷል።
ህዝቡን ከገባበት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ውድቀት ከማውጣት ይልቅ፣ የቡድን ፍላጎትን ለማስጠበቅ ሲባል የተወሰደው ይህ እርምጃ በክልሉ ያለውን አስተዳደራዊ መዋቅር ያፈረሰና የትግራይን ህዝብ ለባሰ መከራ ያጋለጠ ሆኗል።
ህወሓት የስልጣን ጥሙን ለማርካትና የራሱን ጠባብ ቡድናዊ ፍላጎት ለማስጠበቅ ሲል ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ በመፈጸም ሀገር ለማተራመስ ሌት ተቀን ለፍቷል፡፡
በዚህ ሁሉ ጉዞ ውስጥ ግን ሀገር ወዳዱ፣ ሰላምና ልማትን የሚሻው የትግራይ ህዝብ የቡደኑን እኩይ አካሄድ ተረድቶ በመቃወም ለፌዴራል መንግሥቱና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የድረሱልኝ ጥሪውን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በወሰደው የህግ-ማስከበር እርምጃዎችም፤ ለመጥፋት ተቃርቦ የነበረውን የህገወጥ ቡድኑን የቀረች ተስፋ በማመናመን፤ የትግራይ ክልል አካባቢዎችን በመቆጣጠር ለህዝቡ እፎይታን አምጥቷል፡፡
መከላከያ ሠራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎችም ህዝቡ ያሳየው የሞቀ አቀባበልና የፌደራል መንግሥቱ በአፋጣኝ ወደ ስራ ገብቶ አገልግሎቶች እንዲመለሱ ያሳየው ጉጉት፤ ምን ያህል በህገ ወጥ ቡድኑ በደል ስር እንደነበር ማሳያ ሆኗል፡፡
የሀገርን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥሉ ርምጃዎችን መውሰዱና ያን ያህል በህዝብ የተጠላ መሆኑ፤ ድርጅቱ ከሀገራዊ እሴቶችና ከህዝብ ጥቅም ሙሉ በሙሉ መራቁን የሚያረጋግጥ ነው።
በትግራይ ክልል አሁን የሰላም አየር መተንፈስ ጀምሯል፤ እንደተቀሩት ኢትዮጵያዊ እህት ወንድሞቹ በህገወጡ ህወሓት ቡድን ተነፍጎት የነበረውን ሰላምና ልማት በቅርቡ እውን ሊያደርገው ተስፋው ለምልሞ ጉዞውን ጀምሯል፡፡
በመልካም ፈቃዱ

