አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብጽ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ተግዳሮት ከመሆን ይልቅ ተባባሪ ልትሆን ይገባል አሉ የግብጽ ፖለቲካ ተንታኝ ማግዲ ኻሊል።
ግብጻዊው ተንታኝ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ካላት የግጭት ፖሊሲ ወጥታ የባህር በር እንታገኝ ልታግዝ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እጅግ ሰፊ ሕዝብ ያላት ትልቅ ሀገር እንደ መሆኗ መጠን ከጎረቤት ሃገራት ጋር በሰላማዊ መንገድ በሚደረግ ስምምነት የባህር መውጫ የማግኘት ሙሉ ሉዓላዊ መብት እንዳላት አስረድተዋል።
የግብጽ መሪዎች በራዕይና በማስተዋል ታግዘው ኢትዮጵያን ከመቃወም ይልቅ የባህር በር እንድታገኝ ሊረዱ ይገባል ያሉት ተንታኙ አሁን ያለው አካሄድ ከግጭት ወደ ትብብር ሊቀየር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቀይ ባህር ከባቢ ሃገራትም በጋራ ጥቅሞችና በክልላዊ መረጋጋት ዙሪያ ለመወያየትና የተሻለ መግባባት ላይ ለመድረስ የጋራ መድረክ ማዘጋጀት አለባቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

