Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመንግሥት ቁርጠኝነት ለትግራይ ሕዝብ ሰላም

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ግጭት ውስጥ የቆየው የትግራይ ህዝብ በፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ጥረት ወደቀደመ ሰላሙ እየተመለሰ ይገኛል፡፡
ዛሬ ደግሞ የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ምክር ቤት ተመስርቷል፡፡ ይህ ተግባር ለትግራይ ህዝብ እጅግ አስደሳች እና ተስፋ ሰጪ ውሳኔ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ለመፍታት የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት በህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ሳይሳካ ቀርቷል።
ሰላም የማይሻው የህገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የጀመረው አውዳሚ ጦርነት በሽንፈት ተጠናቋቅል።
የትግራይ ሕዝብ የራቀውን ሰላም እንዲጎናጸፍ እንዲሁም ላለፉት በርካታ ዓመታት ያላገኛቸውን የልማት ትሩፋቶች ማግኘት እንዲችል ከግጭት አዙሪት መውጣት አለበት በሚል ሃሳብ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በሕገ መንግሥቱ መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ባስተላለፈው ውሳኔ እና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰጠው ሥልጣን መሠረት የኢፌዴሪ መንግሥት የትግራይ ክልልን የሚያጸና የትግራይ ክልል የፊዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር በዛሬው ዕለት አቋቁሟል፡፡
ይህ የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ለሚቀጥሉት 6 ወራት ትግራይን የሚያስተዳድር ሲሆን የሚያከናውናቸው ተግባራትም የትግራይ ክልልን ሰላም እና መረጋጋት ማስጠበቅ ቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ ሌሎች 9 ተግባራትንም የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ይህ ውሳኔ የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያን በጋራ ለማልማት ለጀመረውን የልማት ጉዞ የትግራይ ክልል ምን ያህል አስፈላጊ አንደሆነ እና የኢትዮጵያውያን አንድነት ለልማቷ እንደሚያግዝ ያሳየበት ተግባር ነው፡፡
መደመር ማለት የራስን ወገን እያገለሉ ከሌሎች ጋር መዛመድ ሳይሆን፤ የራስን ወገን አሳትፎ ከሌሎች ጋር በጋራ መስራት በመሆኑ የመደመር መንግሥት እየሄደበት ያለውን መንገድ አመላካች ነው፡፡
ይህ ውሳኔ የክልሉን ሰላም የሚያስጠበቅ፣ የተጀመሩ እና የተቋረጡ የልማት ስራዎችን የሚያስቀጥል፣ የትግራይን ሕዝብ ከሌሎች እህት ወንድሞቹ ጋር የሚያቀራርብ፣ የክልሉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ፣ የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽል እና የመንግሥትን የሰላም ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ በጎ ተግባር ነው፡፡
በእመቤት ሲሳይ
Exit mobile version