አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች ከተማዋን በተለያዩ አደረጃጀት የሚያገለግሉ አመራሮችን መርጠዋል፡፡
የፕሪቶሪያን ስምምነት ተከትሎ የተመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳዳር በሐይል በማፍረስ ሥርዓት አልበኝነትን ያነገሰው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ከትግራይ ሕዝብ ጫንቃ ተወግዷል።
የትግራይን ሕዝብ ብሎም ሀገርን ለብዙ ኪሳራ የዳረገው ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን ከመላው የትግራይ አከባቢዎች መወገዱን ተከትሎ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን እና መሰረት ልማቶችን አውድሟል።
ሕብረተሰቡ መደኛ የመንግሥት አገልግሎት እንዲያገኝና ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ በቀጥታ መሪዎችን እንዲመርጥ እየተደረገ ይገኛል።
በዚህ መሰረት የውቅሮ ከተማ ነዋሪዎች መምህር ገብረመስቀል ኪዳኑን የከተማዋ ከንቲባ አድርገው ሲመርጡ ሌሎች አራት የሥራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።
እነዚህ የተመረጡ አስተዳዳሪዎች በትግራይ መደበኛ ምርጫ እስከሚካሄድ ከ6 እስከ 8 ወራት ድረስ የሚቆዩ ናቸው።

