Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያና የዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የግል ኢንቨስትመንትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማክታር ዲዮፕ ጋር በዋና ዋና የግል ዘርፍ ልማቶች ላይ ያለውን ትብብር ለማጠናከር ተወያይቷል።
ምክክሩ በባንኮክ ታይላንድ እየተካሄደ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡
ውይይቱ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች፤ በተለይም በተመጣጣኝ የቤቶች ልማት፣ በኃይል ማስተላለፊያ እና በግብርና መሪ ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ የግል ኢንቨስትመንትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።
ስብሰባው ኢትዮጵያ የመንግሥትን የልማት ኢንቨስትመንት የሚያግዝ ዓለም አቀፍ የግል ካፒታልን ለመሳብ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ጥረት የሚያሳይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ይህም ሀገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን እና የመሠረተ ልማት ግንባታውን በዘላቂነት ለማስቀጠል ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል፡፡
Exit mobile version