አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የትምህርት ሚኒስትሩ አማካሪ ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መደበኛ የትምህርት ሥራ ለመግባት ያላቸውን አጠቃላይ የዝግጁነት ሁኔታ ለመገምገም መቐለ ከተማ ገብተዋል።
ክንደያ ገብረሕይወት (ፕ/ር) በሚኖራቸው ቆይታ በትግራይ ክልል የሚገኙ አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመማር ማስተማር ሥራቸውን ለመጀመር ያላቸውን አጠቃላይ ዝግጁነት በዝርዝር የሚገመግሙ ይሆናል።
ይህ ግምገማ ዩኒቨርሲቲዎቹ በተሟላ የሰው ኃይል፣ የመሠረተ ልማትና የሎጂስቲክስ ዝግጅት ወደ መደበኛ የትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ያሉ መልካም ሁኔታዎችንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመለየት ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

