Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዩኒቨርሲቲው በዲሲፕሊን የታነጸ ሠራዊት የማፍራቱን ሒደት ያጠናክራል – አቶ መሃመድ ኢድሪስ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩኒቨርሲቲው በዲሲፕሊን የታነጸ ሠራዊት የማፍራቱን ሒደት ያጠናክራል አሉ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር መሐመድ ኢድሪስ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዲየር ጀነራል ከበደ ረጋሳ ዩኒቨርሲቲው ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ባከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች፣ በትምህርትና ሥልጠና ጥራት፣ በምርምር ውጤቶች፣ በመከላከያ ቴክኖሎጂ ፈጠራና በዓለም አቀፍ ትስስር የተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶችን አብራርተዋል።
የመከላከያ ሚኒስትር መሀመድ ኢድሪስ አጠቃላይ የተመለከቱት የስራ አፈፃፀም ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ተቋም ከመሆን ባለፈ፤ ለመከላከያ ሠራዊቱ ብቁ የሰው ኃይል የሚያፈራ፣ የምርምር ውጤቶችን ወደ ተግባር የሚቀይርና የሀገር ውስጥ የመከላከያ ቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ የሚሠራ ስትራቴጂያዊ ተቋም መሆኑን እንዳረጋገጠላቸው ገልፀዋል።
የመከላከያ ትምህርት ተቋም ዘላቂ ስኬት የሚለካው በተመረቁ ተማሪዎችና በተከናወኑ ምርምሮች ብቻ ሳይሆን፣ ውጤቶቹ ለሠራዊቱ የተልዕኮ አፈጻጸምና ለሀገራዊ የመከላከያ አቅም በሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጭምር ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በዘመናዊ ማዕከላዊ ላቦራቶሪ በሚሰጣቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ በግብርና፣ በመኖ ማቀነባበርና በችግኝ ልማት ያሳየውን አበረርክቶ በማድነቅ፣ የገቢ ማስገኛ አቅሙን የሚያሳድጉ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አጽንኦት መስጠታቸውን ከመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
Exit mobile version