Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ከመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ህዝባዊ ውይይት አካሂዷል።

የውይይት መድረኩ ዓላማ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ከህዝቡ ጋር ለመወያየትና የተለያዩ ማኅበረሰባዊ ክፍሎችን በሚያሳትፍ መልኩ ሃሳብና አስተያየቶችን ለመለዋወጥ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የትግራይ ክልል የፌዴራል መንግሥት ባለአደራ አስተዳደር ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 ንዑስ አንቀጽ 9 እና በአዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2(ለ) መሠረት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ውሳኔ ማስተላለፉና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥልጣን መሰጠቱና ውሳኔው ወደ ተግባር መግባቱ ይታወሳል።

Exit mobile version