Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በግብርናዉ ዘርፍ ያለዉን አቅም፣ ፀጋና ቴክኖሎጂ ማቀናጀት ይገባል -የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በግብርናዉ ዘርፍ ያለዉን አቅም፣ ፀጋና ምቹ ቴክኖሎጂ ማቀናጀት ይገባል አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር)፡፡
የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ይህንን ያሉት በክልሉ በዘንድሮ የተቀናጀ የግብርና ንቅናቄ ውጤታማ የሆኑ አርሶ አደሮችን ማሳ በጎበኙበት ወቅት ነው።
አክለውም የግብርና ሽግግር ስኬት እንዲረጋገጥ የሀገር ስልጣኔና ልዕልና እንዲፀና በግብርናዉ ዘርፍ ያለዉን አቅም፣ ፀጋና ምቹ ቴክኖሎጂ ማቀናጀት ይገባል ብለዋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት 4 ሺህ 600 በላይ ሄክታር ላይ የነበረዉን ባህር ዛፍ በማንሳት በቡና እና ፍራፍሬ ተክሎች የተተኩ ሲሆን በዚህም አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትናቸዉን ከማረጋገጥ ባለፈ ለገበያ የሚሆን ትርፍ ምርትን ማምረት ችለዋል።
በክልሉ በመደመር መንግሥት መርህ መሰረት በግብርናው ስራ ትጋትን በመጨመር ለተሻለ ምርታማነት መረባረብ ትኩረት አግኝቷል።
በጌታቸዉ ሙለታ
Exit mobile version