አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ3ኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ምሽት ዘጠኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
የጀርመኑ ክለብ ባየርን ሙኒክ በሜዳው አልያንዝ አሬና ምሽት 4 ሰዓት ላይ የእንግሊዙን ክለብ አርሰናል ያስተናግዳል፡፡
ባየርን ሙኒክ በውድድር ዓመቱ በሻምፒየንስ ሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት ሁለት ጨዋታዎች አንዱን አሸንፎ፤ በአንዱ አቻ መለያየቱ ይታወሳል፡፡
በአሰልጣኝ ቪንሰንት ኮምፓኒ የሚመራው በሻምፒንስ ሊጉ ከአቻ ውጤት መልስ ወደ ድል ለመምጣት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በጨዋታው የባየርን ሙኒክ ቁልፍ ተጫዋች የሆነው ፈረንሳዊው ኮከብ ኦሊሴ በቀይ ካርድ ምክንያት ከዛሬው ጨዋታ ውጪ ነው፡፡
ጆሽዋ ኪሚች ሌላኛው በምሽቱ ጨዋታ ለባየርን ሙኒክ ግልጋሎት የማይሰጠው ተጫዋች ነው፡፡
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዚህ የውድድር ዓመት በሻምፒየንስ ሊጉ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡
አርሰናል በሻምፒየንስ ሊጉ ተከታታይ ሦስተኛ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ሁለቱ ቡድኖች እርስ በርስ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አርሰናል ሁለቱን ሲያሸንፍ፤ ባየርን ሙኒክ በአንዱ ድል አድርጎ በአንዱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ሪያል ማድሪድ በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናባው ከአርቢ ሌብዚሽ ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ሪያል ማድሪድ በሻምፒየንስ ሊጉ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ኢንተር ሚላን ከሻካታር ዶኔስክ፣ አስቶንቪላ ከቫይኪንግ፣ ሪያል ቤቲስ ከፌይኖርድ፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን ከላስክ እንዲሁም ክለብ ብሩዥ ከሌንስ ሌሎች ምሽት 4 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ከእነዚህ ጨዋታዎች አስቀድሞ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ከኮሞ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
አስቸጋሪ የውድድር ዓመት እያሳለፈ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በሻምፒየንስ ሊጉ ከአትሌቲኮ ማድሪድ ሽንፈት መልስ ወደ ድል ለመምጣት የሚያደርገው ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ ሊል ከጋላታሳራይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

