Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ነጋሽ ተወልደ የዓዲግራት ከተማ ከንቲባ ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ነጋሽ ተወልደ የዓዲግራት ከተማ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት አስተዳዳሪዎቻቸውን መርጠዋል፡፡
የምርጫው ሂደት የአካባቢያቸውን አስተዳደር በቀጥታ በድምፃቸው እንዲመርጡና በአስተዳደሩ ላይ የሕዝብ ተሳትፎን እንዲያሳድጉ የሚያስችል ተነሳሽነትን የፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
በቀጥታ የተካሄደው የአስተዳዳሪዎች ምርጫ ዓላማም የአመራሩን ተጠያቂነት ማሳደግና የአካባቢ አስተዳደሩ በነዋሪዎች ፍላጎትና ተሳትፎ ላይ እንዲመሠረት ማድረግ ነው።
በምርጫው ሂደት መሠረትም አምስት አባላት ያሉት አስተዳደር የተቋቋመ ሲሆን፣ አቶ ነጋሽ ተወልደ የዓዲግራት ከተማ ከንቲባ ሆነው ተመርጠዋል።
በቀጥታ በሕዝብ የተመረጠው ይህ አስተዳደር መደበኛ ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ ለስድስት ወራት በሥራ ላይ እንደሚቆይ ተመላክቷል።
Exit mobile version