አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ፀረ ሰላም ኃይሎችን የሚያወግዝ እና ሰላምን የሚያፀና ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
ሰልፈኞቹ የሰላምን አስፈላጊነት የሚገልፁ መፈክሮችን በማሰማት ህዝባዊ አንድነታቸውን እና ለሰላም ያላቸውን ጽኑ አቋም አሳይተዋል።
በሰልፉ ላይ የተገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ፀረ ሰላም ኃይሎች ህዝብን ለመበታተን እና የልማት ሥራዎችን ለማደናቀፍ የሚደርጉትን እንቅስቃሴ አውግዘዋል፡፡
ሰላም የልማት እና የዕድገት መሰረት በመሆኑ ህዝቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመሆን ሰላሙን በንቃት መጠበቅ እንዳለበት መልዕክት ማስተላለፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

