አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 14፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት ለተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።
ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ÷ ይህ የሩጫ ውድድር በስኬት እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጾ የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራው ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በዚህም ሩጫው ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች፦
👉 ከቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
👉 ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
👉 ከጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
👉 ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
👉 ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
👉 ከትምባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
👉 ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
👉 ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
👉 ከቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
👉 ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
👉 ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
👉 ከሐራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል
👉 ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
👉 ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡
በውድድሩ መስመር ግራና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

