አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 12ኛው የጣና ፎረም የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቅቋል።
ላለፉት ቀናት በባሕር ዳር ከተማ በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሲካሄድ የቆየው 12ኛው የጣና ፎረም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል።
ፎረሙ «አፍሪካን ወደ ሰላም የሚወስዱ መንገዶች፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጂኦ-ፖለቲካ ሽግግር» በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ሲሆን፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ምሁራን በተገኙበት በአህጉራዊ ፈተናዎች እና የመፍትሔ ሐሳቦች ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዷል።
በመድረኩ ማጠቃለያም ለአፍሪካውያን ዘላቂ ሰላም፣ ጠንካራ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የተረጋጋ የጂኦ-ፖለቲካ ሽግግር ማምጣት የሚያስችሉ ተግባራዊ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በደሳለኝ ቢራራ

