አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2026 የባሎንዶር ሽልማት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ምሽት በለንደን ይካሄዳል፡፡
ሃሪ ኬን፣ ኪሊያን ምባፔ፣ ላሚን ያማል እና ኦስማን ዴምቤሌ ለዘንድሮው የባሎንዶር ሽልማት ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ሊዮኔል ሜሲ፣ ጅድ ቤሊንግሃም፣ ኦሊሴ፣ ሃላንድ፣ ዴክላን ራይስ፣ ክቫረትስኬሊያ፣ ቪኒሸስ ጁኒየር፣ ቪቲኒሃ፣ ሮድሪ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ የመሳሰሉ ተጫዋቾች የመጨረሻ 30 ዕጩዎች ውስጥ ይገኙበታል፡፡
ዳዮት ኡፓሜካኖ፣ ዊሊያም ሳሊባ፣ ፌራን ቶሬስ፣ ማርኪኒዮስ፣ ፓቾ፣ ጆኣኦ ኔቬስ፣ ኑኖ ሜንዴስ፣ ላውታሮ ማርቲኔዝ፣ ሳዲዮ ማኔ፣ አሽራፍ ሃኪሚ፣ ጋብሬል ማጋሌሽ፣ ፋቢያን ሩሂዝ፣ ጁሊያን ኪኖንስ፣ ሉዊስ ዲያዝ፣ ማርክ ኩኩሬያ እና ኩባርሲ ሌሎች የሽልማቱ እጩ ተጫዋቾች ናቸው፡፡
70ኛው የባሎንደር ሽልማት ሥነ ሥርዓት ዛሬ ምሽት 3 ሰዓት ላይ በለንደን የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የባሎንዶር የሽልማት ሥነ ሥርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ ከፈረንሳይ ውጪ ይደረጋል፡፡
በባሎንዶር ሽልማት ታሪክ ሊዮኔል ሜሲ 8 ጊዜ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ደግሞ 5 ጊዜ በማሸነፍ በርካታ ጊዜ በመድረኩ መድመቅ የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

