Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ ክስ ለመመስረት 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ጠየቀ።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ካቀረባቸው 15 የቅድመ ምርመራ ምስክሮች ውስጥ 10 አሰምቶ ቀሪው ይበቃኛል በማለት፤ አቶ ጃዋርን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ እስክመሰርትባቸው የክስ መመስረቻ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች በበኩላቸው ለአቃቤ ህግ ክስ መመስረቻ 15 ቀን ሊሰጥ አይገባም ያሉ ሲሆን፥ ለደንበኞቻቸውም የዋስትና ጥያቄ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም አቃቤ ህግ በጠየቀው የ15 ቀን ክስ መመስረቻ እና የተጠርጣሪዎች የዋስትና ጥያቄን መርምሮ ትእዛዝ ለመስጠት ለጳጉሜ 2 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

Exit mobile version