Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፀረ ሽምቅ ውጊያን መመከት የሚችል አቅምና ቁመና የመከላከያ ሠራዊቱ መገለጫ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና በሰለጠነ የሰው ሀይል የተደራጀ በመሆኑ ፀረ ሽምቅ ውጊያን መመከት የሚችል አቅምና ቁመና ፈጥሯል።
መከላከያ ሠራዊት ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ እያከናወናቸው ያሉት ሀገርን ከጠላት የመጠበቅ ተግባር ይህንን እውነታ ያሳያል።
በውስጥም በውጪም ሀገርን ለማወክ የተደራጁ ፀረ-ሰላም ሀይሎች የሚፈጥሩት ትንኮሳና የሽምቅ ውጊያ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም የማስተጓጓል ብቃት የሌለው መሆኑ በተደጋጋሚ ታይቷል።
በዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ እንዲሁም ቀጣናዊ የፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በቂ ዕውቀት ያለው ሠራዊት መፈጠሩ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት የሚያስችል አቅምን አዳብሯል።
በተለይም ከፍተኛ መኮንኖች በተመደቡበት የስራ መስክ የተሻለ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ሠራዊቱ የላቀ ቁመና እንዲኖረው በትኩረት መስራታቸው ውጤቱን የላቀ ያደርገዋል።
ሠራዊቱ በቅርቡ ያሳየው ልዩ ብቃት ኢትዮጵያ በወታደራዊ አቅሟ የላቀ ደረጃ ላይ መድረሷን ያስገነዘበ ከመሆኑም በላይ ጠላቶቿን አስደንግጧል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት 119ኛ ዓመት በዓል በተከበረበት ወቅት ያስተላለፉት መልዕክትም ይህንን የሚያሳይ ነው።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በመልዕክታቸው፤ ሊያፈርሱት የከጀሉትን ያፈርሳል እንጂ በመከላከያ ሠራዊት መቃብር ላይ የምትመሰርቱት የሽግግር መንግሥት የለም ብለዋል።
ለሰላም እጅ ስጡ፣ ፖለቲካ እና ስልጣንን ከፈለጋችሁ ተደራጁና በሰላማዊ መንገድ ተወዳደሩ። ከባዕዳን ጋር ሆናችሁ በአቋራጭ ስልጣንን ለማግኘት መሞከር ከንቱ ምኞት ነው በማለት ገልጸው፤ በጫካ መንገድ ሞክራችሁ ሲያቅታችሁ መከላከያን ለማፍረስ አትንጠራሩ፤ መከላከያ የጠላትን ሴራ ያፈርሳል እንጂ አይፈርስም ሲሉ አረጋግጠዋል።
ሠራዊቱ ሀገርን ያኮራ ስራ ሠርቷል፣ እየሰራ ይገኛል። በቀጣይም የኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ዘብ መሆኑን አጠናክሮ ይቀጥላል።
ሠራዊቱ በአሁኑ ወቅት ከየትኛውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በባህር፣ በየብስና በአየር በየትኛውም ቦታና ወቅት ውስብስብ ግዳጆችን የመፈፀም አቅሙን አጠናክሯል። ይህንን እውነታ የኢትዮጵያ ጠላቶች በውል ተገንዝበዋል።
Exit mobile version