አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ (አይሲአርሲ) የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ማማዱ ሶው እና ልዑካቸው ጋር ተወያይተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በውይይታቸው÷ አይሲአርሲ ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ረጅም ዘመን ያስቆጠረ አጋርነት አመስግነዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በሰብዓዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

