አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተባበሩት መንግሥታት የሰው ሰፈራ ፕሮግራም ጋር የአዲስ አበባን ዘላቂ ልማት ለማጠናከር የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ በከተማ መረጃ አሰባሰብና ትንተና፣ በልማት ውጤቶች ክትትል፣ በ11ኛው የመዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት፣ በተመጣጣኝ ዋጋ የቤት አቅርቦት እና ከCOP32 ጋር በተያያዙ የከተማ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
ትብብሩ የከተማ አስተዳደርን ለማሻሻል፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና ለነዋሪዎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ ለማጠናከር የሚያግዝ ነዉ።

