Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፋና ላምሮት ምዕራፍ 23 ፍፃሜ!

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 17፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ላለፉት ሶስት ወራት በጠንካራ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት የምዕራፍ 23 ውድድር ቅዳሜ ፍፃሜውን ያደርጋል።
16 ተወዳዳሪዎችን ይዞ የጀመረው የምዕራፍ 23 ውድድር በየሳምንቱ አንድ ተወዳዳሪ እየተሰናበተ አራቱ ተወዳዳሪዎች ለፍፃሜ ደርሰዋል።
በቅርቡ ወደ ሚጀመረው እና ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት ወደ ተዘጋጀለት 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ያረጋገጡት አራቱ የዚህ ምዕራፍ የፍፃሜ ተወዳዳሪዎች ዳዊት አታላይ፣ ሀይለየሱስ ታደገ፣ ሀይለማርያም ተገኑ እና በረከት መስፍን ለፍፃሜው የሚፋለሙ ናቸው።
ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ለዚህ የፍፃሜ ውድድር የ 1 ሚሊየን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል።
ማን የምዕራፍ 23 ኮከብ ሆኖ ያጠናቅቅ ይሆን? የፍፃሜ ውድድሩን ቅዳሜ 6:00 ላይ በሁለቱም የፋና ቴሌቭዥን ቻናሎች እና በፋና የዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን።
በለምለም ዮሐንስ
Exit mobile version