Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ወደ መገጭ ግድብ ተጨመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2019 ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በተመረቀው የመገጭ ግድብ የቆሮሶ ዝርያ ያላቸው 125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶች ተጨምረዋል።
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ባለሙያ አቶ አበበ ፈንታሁን እንደገለጹት፤ ክልሉ ያለውን የዓሳ ሀብት ልማት ሰፊ አቅም ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል፡፡
በዚህም ያለውን የውሃ አማራጭ በመጠቀም የዓሳ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ወደ መገጭ ግድብ 125 ሺህ የዓሳ ጫጩቶችን የመልቀቅ ሥራ የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል።
በክልሉ ባለፈው በጀት ዓመት 43 ሺህ ቶን በላይ የዓሳ ምርት መገኘቱን አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ በዘርፉ የስራ ዕድል ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልጸው፤ በዓሳ ሃብት ልማት ለ20 ሺህ ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል ብለዋል።
በክልሉ በሚገኙ 10 ሀይቆች፣ 40 ግድቦች እና 20 ወንዞች ላይ የዓሳ ሀብት ልማት እየተከናወነ እንደሚገኝም ማብራታቸውን የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።
Exit mobile version