አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ደህንነትን ለማስጠበቅ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ስልቶችን እየተገበረ ይገኛል አሉ አሉ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሦስተኛው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ወር ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ የባንኩን ደህንነት በዘመናዊ መልኩ ለመጠበቅ የሚያስችሉ «የአየር ኃይል መከላከያ»፣ «ዜሮ ትረስት» እና «የቀጥታ ዝግጅት» የተሰኙ ቁልፍ የሳይበር መከላከያ ስልቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባንኩ ከ80 ዓመታት በላይ በቆየው ጉዞው በገበያ መዋዠቆችና በፖለቲካ ለውጦች ሳይበገር ለሀገርና ለሕዝብ ታማኝ አገልጋይ ሆኖ ቆይቷል።
የሕብረተሰቡን ሰፊ እምነትና ተደራሽነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የዲጂታል ደህንነትን ማጠናከር የህልውና ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።
በዲጂታል ዘመን የተገነባው ሕዝባዊ እምነት በጥቂት ሰከንዶች ውስጥ በሳይበር ጥቃት አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል በመገንዘብ ባንኩ የሚከተላቸው የመከላከያ አሰራሮች ማንኛውንም ስጋትና ጥቃት ወደ ዋናው የባንክ ሥርዓት ሳይደርስ አስቀድሞ የሚይዝ እና የሚያከሽፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን በድርጅቱ እየተከበረ ይገኛል።
የሳይበር ደህንነትን አስፈላጊነት ለሕዝቡ ማስገንዘብ፣ ደንበኞች የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን በደህንነት እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር እንዲሁም ከሳይበር ጥቃቶችና ከዲጂታል ማጭበርበሮች ራሳቸውን የሚጠብቁባቸውን ዘዴዎች ማስተዋወቅ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።
በቅድስት ተስፋዬ

