አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በዓለም አቀፉ የወንጀል ፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ዋና ፀሐፊ ቫልዴሲ ኡርኪዛ የተመራ የልዑካን ቡድን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤልና በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታምራት ሙሉጌታ (ዶ/ር) አቀባበል ተደርጎለታል።
በቆይታቸውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስን ዋና መሥሪያ ቤት እንደሚጎበኙ እና ለኢንተርፖል አባል ሀገራት የሕግ አስከባሪዎች ጥራት ያለው ስልጠና በመስጠት ከሚታወቀው የኢንተርፖል ግሎባል አካዳሚ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ይፈራረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።

