Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን መቀበል ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል፡፡
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መስራችና የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሎሬት ምትኩ ኃይለ (ፕ/ር) አዳዲስ ተማሪዎችን እንኳን ወደ እውቀት ቤታችሁ፣ ወደ ሁለተኛ መኖሪያቹ በሰላም መጣችሁ በማለት አቀባበል አድርገዋል።
የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዓብደልቃድር ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲያችን ለእናንተ እንደ አባት፣ እንደ እናት እንዲሁም እንደ ቤተሰብ ሆኖ የነገ ተስፋችሁን ለማቅናት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡
ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ፣ በዕውቀት እና በበጎ ሥነ ምግባር እንዲታነጹ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው እየተቀበለ የሚገኘው ከ1 ሺህ 800 በላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ስለመሆኑም ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
Exit mobile version