አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በ9ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት አንድ ጨዋታ ይደረጋል፡፡
በዚህም ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ አርሰናልን ያስተናግዳል፡፡
ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ድል ያደረገው ሊቨርፑል 3ኛ ተከታታይ ድሉን በሊጉ ለማሳካት ወደ ሜዳ ይገባል፡፡
በአንዶኒ ኢራኦላ የሚመራው ሊቨርፑል በ15 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን ከፍ በማድረግ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡
ተጋጣሚው አርሰናል በበኩሉ በፍሊትውድ ታውን ከካራባኦ ካፕ ከተሰናበተ በኋላ የሚያደርገው የሊግ ጨዋታው ነው፡፡
በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ነጥቡን 24 በማድረስ ሊጉን መምራት የሚጀምር ይሆናል፡፡
ትናንት በተደረጉ የሊጉ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መሸነፉ ይታወቃል፡፡

