Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትብብርና በመደመር የወደፊት ዕድላችንን በጋራ መገንባት አለብን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በትብብርና በመደመር የወደፊት ዕድላችንን በጋራ መገንባት አለብን አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ በዓለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) የተፃፈው “ምሉዕነት” የተሰኘው መጽሐፍ የግለሰብን ውስጣዊ እድገት ከማኅበረሰብ ጥንካሬ ጋር በማገናኘት፣ አካታች ፖለቲካን፣ የጋራ ብልጽግናንና ባህላዊ ብዝሃነትን የሚያቀናጅ ጥልቅ ሐሳብ ያቀርባል።
ዋናው መልዕክቱም ልዩነታችንን የመለያየት ምክንያት ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ አድርገን፣ በመተማመን፣ በትብብርና በመደመር የጋራ የወደፊት ዕድላችንን በጋራ መገንባት እንዳለብን ያስገነዝባል ሲሉም አመልክተዋል፡፡
ይህም በመንግሥት ብቻ ሳይሆን፤ በሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትና ተሳትፎ የሚሳካ ግብ በመሆኑ መጽሐፉ ለሀገራችን የጋራ እውቀትና ለተሻለ ማኅበረሰብ ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ እንጠቀምበት ብለዋል፡፡
ልዩነታችንን አክብረን፣ አቅማችንን አቀናጅተን፣ በመደመርና በትብብር የጋራ ብልጽግናን እንገንባ ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
Exit mobile version