አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በመቐለ ከተማ በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማስፈጸም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር) በተገኙበት የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡
በትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ሥር የሚገኘው የመቐለ ከተማ ባለአደራ አስተዳደር ባካሄደው ስብሰባ በከተማዋ የደረሰውን ውድመት ለማስተካከል፣ የተቋማትን አቅም ለማጠናከርና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ዙሪያ ተወያይቷል።
በውይይቱም የከተማዋን መልሶ ግንባታና የልማት ሥራዎች ማፋጠን፣ የተቋማትን የሥራ አቅም ማሳደግ፣ እንዲሁም ነዋሪዎች የሚያስፈልጋቸውን አገልግሎቶች ያለ መዘግየት እንዲያገኙ ማስቻል የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑ ተመላክቷል።
እስካሁን በከተማዋ የተከናወኑ አበይት ሥራዎች የተገመገሙ ሲሆን፤ አፋጣኝ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን በመለየት ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ በቀጣይ የሚከናወኑ ሥራዎችን በተቀናጀ መልኩ ለማስፈጸም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በግዛቸው ግርማዬ

