አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተገልጋይ እርካታን የሚያረጋግጡ አሰራሮችን በጥራት ለመተግበር በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ።
በደብረ ብርሃን ከተማ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የኮሪደር ልማት እንዲሁም የደረቅ እና የፈሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በፕሮጀክቶቹ ምረቃ ወቅት እንዳሉት፤ የተገልጋይ እርካታን የሚያረጋግጡ አሰራሮችን በጥራት ለመተግበር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።
በዛሬው ዕለት የተመረቁ ፕሮጀክቶችም የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ እና ውብ መኖሪያን ለመፍጠር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ነው ያሉት።
የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፤ ለአገልግሎት የበቁት ፕሮጀክቶች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ የሚያስችሉ መሆናቸውን አንስተዋል።
የከተማዋን እድገት እና የነዋሪውን ፍላጎት ከመመለስ አኳያም ከፍተኛ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል።
በጀማል አህመድ

