Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ ቻይና ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ ቻይና የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች አሉ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ቼን ሃይ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የኢትዮጵያ እና የቻይና ስትራቴጂካዊ ትብብር የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል በሚቻልባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን፣ በተለይም በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በአቅም ግንባታ ዘርፎች ያላቸውን አጋርነት ለማሳደግ ተስማምተዋል።

የቻይናው አምባሳደር ቼን ሃይ በዚሁ ወቅት ሀገራቸው የመደመር መንግሥት ትልሞች ውጤታማ እንዲሆኑ የምታደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።

Exit mobile version