Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከቻይና የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋን ጋር ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የአፍሪካ ጉዳዮች የቻይና ልዩ መልዕክተኛ ሊዩ ሺያንፋንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ዙሪያም ሐሳብ መክረዋል።
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ላይ ለልዩ መልዕክተኛው ገለጻ አድርገዋል፡፡
ሊዩ ሺያንፋ፤ በበኩላቸው ሀገራቸው በአፍሪካ ሰላምና ደህንነትን እንዲሰፍን የሚኖራትን በጎ ሚና እና የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ለመቀጠል ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
Exit mobile version