Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው አሉ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)።
ሚኒስትሩ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳነሱት፤ ኢትዮጵያ ግድቦችን እንዳትሰራ የማድረግ ሥራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል።
ይህ ሥራቸው ኢትዮጵያን ይበልጥ አንድ እንዳደረገ ገልጸው አንድ ከመሆንም አልፎ በጋራ መቆም እንደምንችል የሕዳሴ ግድብ ማሳያችን ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ማንም ሳያግዛት በራሷ አቅም የገነባችው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም ከቻሉ ምን ያህል ማሸነፍ እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
የውሀ ሀብታችንን እንዳናለማ የሚደረጉ ጫናዎችና ሴራዎች ኢትዮጵያውያንን ይበልጥ አንድ እንዲሆኑ እና በጋራ እንዲቆሙ እንዳደረጋቸው አመላክተዋል።
የግብጽና የተከፋዮች ጩኸት እዚህም እዚያም ቢኖርም፤ ኢትዮጵያውያን ግን በታላቅ ርብርብ ታሪክ መስራታቸውን አረጋግጠዋል ነው ያሉት።
ታሪካዊ ጠላቶች ሀብታችንን እንዳናለማ ሲያጠለሹና ግጭቶችን ከጀርባ በመሆን በማባባስ ብዙ መስዋዕትነት እንዲከፈል ማድረጋቸውን ገልጽው ይህን ሁሉ ፈተና አልፈን የድል ምዕራፍ ላይ ደርሰናል ብለዋል።
በመልካም ፈቃዱ
Exit mobile version