አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) አብዛኛው የውኃ ድርሻ ለግብጽ እንዲሄድ መደረጉ ህሊና ያለው ሰው የሚቀበለው አይደለም አሉ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)::
የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳነሱት፤ የሱዳን ወገኖችና ምሁራን ሊገነዘቡት የሚገባው ነባሩ የቅኝ ግዛት ውል ሱዳኖችንም ጭምር አስሮ ያስቀመጠ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ስታድግ ብቻዋን እንዳልሆነ ያነሱት ሚኒስትሩ የምታድገው ቀጣናውን ይዛ ለመነሳት እንደሆነ አመልክተዋል።
የውኃው አጠቃቀም ፍትሃዊ እንዳልሆነ እና አብዛኛው ድርሻ ለግብጽ እንዲሄድ መደረጉ ህሊና ያለው ሰው የሚቀበለው አለመሆኑን አንስተዋል፡፡
ግብጾች የኢትዮጵያን የዕድገት ፍጥነት እንደሚፈሩት በመግለጽ ኢትዮጵያ ለእድገት በምታደርገው ጉዞ ሁልጊዜም ለጎረቤቶቿ ቅድሚያ የሚሰጥ መሆኑ አመልክተዋል።
አክለውም የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ቀጣናውን በጋራ ማሳደግ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እና የመደመር እሳቤም የሚያስተምረው ይሄንን እንደሆነ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል።
በመልካም ፈቃዱ

