Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፍርድ ቤቶች ባለፈው በጀት ዓመት ለ140 ሺህ መዝገቦች ውሳኔ ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ፍርድ ቤቶች ባለፈው በጀት ዓመት ለ140 ሺህ መዝገቦች ውሳኔ ሰጡ ፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች አምስተኛ መደበኛ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ በዚሁ ወቅት ባቀረቡት ሪፖርት ”ባለፈው በጀት ዓመት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች 140 ሺህ መዝገቦች ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል”ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በፌደራል ፍርድ ቤቶች የሪፎረም ትግበራ እንደተከናወነ ገልጸው÷ የክልል ፍርድ ቤቶችም በሪፎርም ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል ፍርድ ቤቶችን በከፊል ክፍት በማድረግ የዳኝነት አገልግሎት መሰጠቱንም አስታውቀዋል፡፡

በዚህም 7 ሺህ መዝገቦች እልባት ማግኘታቸውንም ወይዘሮ መዓዛ ተናግረዋል፡፡

በጉባዔው የአገሪቱ የዳኝነት ነፃነት ሁኔታና ፍርድ ቤቶች የኮቪድ 19 ወረርሸኝን ለመከላከል ያከናወኗቸው ተግባራት እንደሚዳሰሱ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

Exit mobile version