Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ግብጽ የአስዋን ግድብን ስትገነባ ከ100 ሺህ በላይ ሱዳናውያንን አፈናቅላለች – ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ግብጽ የአስዋን ግድብን ስትገነባ ከ100 ሺህ በላይ ሱዳናውያንን አፈናቅላለች አሉ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡
ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ግብጽ በአንድ አፍ ሁለት ምላስ እየሆነች ኢትዮጵያን ጠንቅቆ ካለማወቅ የተለያዩ ውንጀላዎችን ብታቀርብም ምንም ማስረጃ የላትም ብለዋል፡፡
የፒስ ካናል የሚባል ወደ ሲናይ የሚሄድ ካናል ገንብተው በበረሃ ውስጥ ውሃ ሲያባክኑ እና አስዋንን ገንብተው በቢሊየን የሚቆጠር ሜትር ኪዩብ ውሃ በትነት መልክ ሲያጠፉ የላይኛውን ተፋሰስ ሀገራት አለማማከራቸውን ገልጸዋል፡፡
በአስዋን ግድብ ምክንያት ዛሬ ያሉበት የማይታወቁ ሱዳናውያን መኖራቸውን ጠቁመው፤ ከቤታቸው ተፈናቅለው ቦታቸው የተወሰደባቸውና የጠፉ ብዙ ናቸው ሲሉም አብራርተዋል፡፡
የሱዳናውያን ስልጣኔ መነሻ የሆኑ ሀብቶች በአስዋን ግድብ ተቀብረው መቅረታቸውን አንስተው፤ ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሱዳን ኑቢያ ሰዎች ጠፍተዋል ነው ያሉት፡፡
ይህ ተግባር የሚያሳየው በአቅራቢያቸው ያለውን ማህበረስብ የማጥፋት እና ራሳቸውን ብቻ ለማልማት የመሞከር ሂደት መሆኑን ያሳያል ሲሉም አመልክተዋል፡፡
እኔ ብቻ ልደግ ለሚለው አካሄዳቸው ከዚህ የበለጠ ማስረጃ ሊገኝ አይችልም ብለዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
Exit mobile version