Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ ለወታደራዊ ኤክስፐርቶቹ  አጠቃላይ የሙዚየሙን አሁናዊ ሁኔታ እና ቀጣይ ሊገነባ የታቀደውን ዘመናዊ ወታደራዊ ሙዚየም በተመለከተ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡

‌‎በሙዚየሙ የወታደራዊ ቤተ-መዛግብት እና ቤተ-መጽሐፍት መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ ታደሰ በዚህ ወቅት÷ በቀጣይ በጋራ በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ስለመደረጉ ተናግረዋል።

የኒጀር ወታደራዊ ኤክስፐርቶችበበኩላቸው÷ በኒጀር ተመሳሳይ ወታደራዊ ሙዚየም ለመገንባት መታቀዱን ገልጸው ጉብኝቱ ለግንባታው  ትልቅ ግብዓት እንደሚሆንላቸው ገልጸዋል።

‎የኤክፐርት ቡድኑ መሪው ሲንየር ኮሎኔል ሀምዱ ድጂቦ÷ ጉብኝቱ ስለ ኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ታሪክ የነበራቸውን ግንዛቤ እንዳሰፋው ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም ከሙዚየሙ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ መግለፃቸውን  የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version