አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች አህጉራዊ ጉባኤ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመካሄድ ላይ ነው።
በአዲስ አበባ መካሄድ የጀመረው ይህ ጉባኤ “እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው” በሚል መሪ ሐሳብ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች፣ የገዢና ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች፣ ሚኒስትሮችና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባኤው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባሻገር በሀገር ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ዕድገትና በዘላቂ ልማት ላይ በትብብር እንዲሠሩ የሚያስችሉ ስትራቴጂዎችንና የጋራ አቅጣጫዎችን ለመመስረት ያለመ ነው።
በመሳፍንት ብርሌ

