አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ሀገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅቡል ልማታዊ ሀሳቦችን ወደፊት በማምጣት ለአህጉራዊና ሀገራዊ እድገት ሊሰሩ ይገባል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡
2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ “እድገትን ማስተዳደር፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአፍሪካ ኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ንድፍ አውጪዎች ናቸው” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጉባኤው መሪ ሀሳብ በአህጉሪቱ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያራምዱት ርዕዮተ ዓለም የሕዝብን ህይወት ለማሻሻል ያበረከተውን አስተዋጽኦ ለመረዳት የሚያግዝ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር እሳቤን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ያጋሩ ሲሆን፤ ይህም እያንዳንዱ ዜጋ ለሀገሪቱ እድገት ማበርከት የሚገባውን ሚና መወጣት እንዳለበት የሚያስገነዝብ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ወደ 17 ሚሊየን የሚጠጉ አባላትን ማፍራቱን ገልጸው፤ የመደመር መንግሥት በየትኛውም የፖለቲካ ጎራ የሚገኙ ዜጎች ለሀገር ለሚያበረክቱት አስተዋፅኦ ትኩረት ይሰጣል ነው ያሉት።
በዚህም ፓርቲው የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋትና የተለያዩ እሳቤዎችን ለማስተናገድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 15 በመቶ ያህሉን የፓርላማ መቀመጫ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጉን አንስተዋል፡፡
በሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ማሻሻያው የቴሌኮምና ባንኮች ዘርፍ ለውጭ ክፍት መደረጉ፤ ገበያ ተኮር የውጭ ምንዛሪ ስርዓት መተግበሩንም ተናግረዋል፡፡
ከ53 ሚሊየን የሚበልጡ ዜገች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም የተለያዩ አሰራሮችን

